Yelimizhat : የልምዣት

by Hadis Alemayehu

ETB 1,500.00

Condition: Good
Category: Fiction
Language: Amharic
Publication Year: 1980
Location: Addis Ababa (Akaki kality)
Description

የልምዣት ከሐዲስ አለማየሁ ሶስት ታላላቅ ልብወለዶች አንዱ ነው። ሌሎቹ ፍቅር እስከ መቃብር እና ወንጀለኛው ዳኛ ናቸው።

ወደ የልምዣት ስንመጣ ደመቀች አባቷ ሊሆኑ ለሚችሉ የ50 አመት አዛውንት ስትዳር ገና የስምንት አመት ህጻን ነበረች። ገላዋ ገና ለምንም ያልደረሰ፣ ክፉና ደግ ለይታ የማታውቅ ምስኪን ህጻን ነበረች። ዘወትር ማታ ለጋ ገላዋ፣ በአዛውንት የወሲብ ስሜት ሲታረስ ያድራል። ምሬቱ ሲበዛባት መላ ህይወቷን ከኖረችበት መንደር እብስ ብላ ጠፍታ ከአንድ ልጇ ጋር ወደ አዲስአበባ ትኮበልላለች።

በሻህ ዘለሌን አስታውሰዋለሁ። ግሩም ገፀባህሪ ነው። ለማንኛውም ወንድ አርአያ የሚሆን ነው። ሐቀኛ እና ደፋር ነው ፤ ከአንደበቱ ቆጠብ ያለ።በሻህ በጣሊያን ወረራ ዘመን ጣልያንን አርበድብዷል። በሚስጥር ስሙ "የጨለማው ንጉስ" ነበር። ሐዲስ በላይ ዘለቀን ወስደው በሻህ ዘለሌ በማድረግ ልብወለዳዊ እና ዘለአለማዊ አድርገውታል። የስማቸው የመጀመሪያ ፊደላት በ እና ዘ ከመመሳሰሉ ባሻገር ሁለቱም በጣሊያን ዘመን የሰሩት የጀግንነት ስራ አንድ ያደርጋቸዋል። ከሐዲስ አለማየሁ አይረሴ ገፀ ባህሪያት አንዱ ነው።

ሀዲስ አለማየሁ በተባ ብእራቸው ብዙ ጉዳይ ይዳስሳሉ። መፅሀፉ ብዙ ጉዳዮችን ያነሳል፦ ያላቻ ጋብቻ ፣ ወደ ከተማ ስደት ፣ የባእድ የባህል ወረራ እና ሌሎችም።

ይህ ልብወለድ በፍቅር እስከ መቃብር ደማቅ ጥላ ተሸፍኖ ሳይታይ የቀረ ነው። በታሪኩና በቋንቋው ከፍቅር እስከ መቃብር መገዳደር ባይችልም በራሱ መንገድ ጥሩ ልብወለድ ነው።

Seller Information

Please login to view seller contact details.

Please login to view seller contact details.
Share
Please login to express interest in this book.